ቦታ እንቀያየር ይሆንiii??? [19/08/2010 ዓ.ም 5:27 am]


ምን እየሆንን እንደሆነ ሳስብ ግራ ይገባኛል:: ወንድ ሆኖ ተፈጥሮ ወንድ መሆን አስጠልቶት ሴትለመሆንይዃትናል:: ሴቷ ደግሞ ሴትነት አስጠልቷት የወንድ ልብስ በመልበስ: እንደ ወንድ በመናገር: በመራመድ: እንደ ወንድአክትበማድረግ ወንድ ለመምሰል ትሞክራለች:: ሀገር ውስጥ ያለው ውድ ሀገሩ ኢትዮጵያአስጠልታው”: “ወይ ኢትዮጵያመቸ ይሆን የምላቀቅሽ?” እያለ ከሀገሩ ለመውጣት ሲመኝ ያላየውን አለም ይናፍቃል:: በተቃራኒው ከሀገሩ ውጭ ያለው ውብ ሀገሩ ናፍቃው: ጋራው ሸንተረሩ፣ በጋራ መብላት መጠጣቱ፣ባህሏ፣ ቅርሷ ትዝ እያለው፣ ባርነቱ ሰልችቶትመቸ ወደ ሀገሬ ኢትዮጵያ በተመለስኩ ለሀገሬ አፈር ባበቃኝ!” ይላል:: በቅድስት እምነት ኦርቶዶክስ ውስጥ ያለው በእምነት በምግባር መቆየትሰልችቶትወደ መናፍቃን አዳራሽ ይጎርፋል::እኩሉ ደግሞ አእምሮውን ሽጦ የሚኖርበት እምነት_ቅብ ስጋዊ ሕይወት ሰልችቶት ወደ ቅድስት እምነት ይመጣል:: በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ ያለው ደግሞ በዝማሬ፣ በፀሎት የኖረው መዝሙርሰልችቶት ዘፈን ዘፈን እያለ ወደ አለም ይወጣል:: በዘፈንና በዳንኪራ የቆየው ጫጫታውና ሙዚቃው ሰልችቶት መዝሙርና ፀሎት ናፍቆት፣የተመስጦ ሕይወት መኖር ተመኝቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጣል:: ሰባኪው የተቀበለውን መክሊት ረስቶ ዘረኝነት አስክሮት፣ ፖለቲካው አስጥምሞት መክሊቱን ይቀብራል:: ፖለቲከኛው ደግሞ ክርክሩ፣ ንዝንዙ፣ አድርባይነቱ ሰልችቶት ሁሉንም ጠጥሎ ወደ ምናኔ ሕይወት ይመጣል:: በትዳር ሕይወት ያለው የትዳር ሕይወትሰልችቶት ወንደላጤነትን ይመኛል:: ወንደላጤው ደግሞ  በትዳር ሕይወት ለመኖር ይዃትናል:: ስራ የሌለው ሥራ ለማግኘት ደፋ ቀና ይላል ፈጣሪውን ይለምናል:: ስራ የያዘው ደግሞ ስራው ሰልችቶት አሻግሮ እያየ ስራውን ያማርራል:: ብቸኛው ብቸኝነት መሮት ከእራሱ ጋር ማውራት ሰልችቶት ሰው ሰው አሰኝቶት ህብረትን፥መወያየትን ይናፍቃል:: በህብረት የሚኖረው ደግሞ መተባበር በአፍንጫየ ይውጣ ብሎ ብቸኝነትን ይናፍቃል::.................................. ........................ ................................... ................ ................................ ....................................... ................

 ይህን ሁሉ ሳስብቦታ ተቀያይረን እንሞክረው ይሆንii????” እላለሁ:: ይህ የሆነበት ምክንያት ግን አእምሮአችንና ልቦናችን ጠፍቶብን ስሜታችን ስለሚመራን ነው:: የሰው ልጅ ሙሉ የሚሆነውና ነገሮችን መረዳት የሚችለው አእምሮውን፣ ልቦናውን እና ስሜቱን አስተባብሮ ሲጠቀምበት ነው:: ሰው አእምሮውንና ልቦናውን መጠቀም ሲሳነው ስሜቱን መምራት ይሳነዉና ስሜቱ ይመራዋል::  ስሜቱ ይመራው ደግሞ የማይሆነውን ይመኛል፣ ለመምሰል ይዃትናል፣ መሻገር እንጅ መሻገሪያዉን አያይም:: ማየቱን እንጅ ወርቅ ይሆን ጠጠር አይለይም:: በምክንያት ሳይሆን ሰው አይቶ ይደግፋል፣ መውጣቱን እንጅ መሰላሉን አያይም፣ ደስ ያለውን ያደርጋል: በቶሎ ለመጨበጥ ይሮጣል ሲጨብጠው በቶሎ ይሰለቻል አብዝቶ ስፈልገው የነበረው ሲያገኘው በቶሎ አብዝቶ ይጠለዋል:: ዘመነ ስሜታዊነት፣ ይብቃኝ ቻው ...................M.T

Comments