..“አልተግባብቶም”


አካባቢው በጫጫታና በሁከት ተሞልቷል:: ሁሉም መናገራቸውን እንጅ ምን እንደሚናገሩ፣ምን እንደሚነገር፣ ማን እንደሚናገር አያዳምጡም:: ብቻ አፋቸው ያመጣውን፣ ስሜታቸው የሚያዝዛቸውን ይናገራሉ:: ስሜታችው እየጋለ ወደ ድብድብ ሊያመራ ይመስላል:: ሁሉም የኔ ነው ትክክል! የኔ ነው ትክክል! በሚል ስሜት ተውጠው የሌላው ሀሳብ አይጥመውም፥ አያዳምጠውምም:: ከመካከላቸው አንዱይህ እኮብርነው ምን ነካችሁ? ይህ እኮ ጫማ፣ ልብስ፣ቲማቲም፣ሽንኩርት የምንገዛበት ብር እኮ ነውይላል:: አንዱ ደግሞ ፀጉሩን እየፈተለ በአንድ እጁ ሱሪውን ይዞኧረ ነው ምን ሆናችኋል? ይህ እኮጨላነው! ቀፍላችሁ አታውቁም እንዴ?” ይላል:: ሌላው ደግሞ በሲጋራና በጫት የበለዙ ጥርሶቹን እያሳየኧረ ፍሬንድ አምፖላችሁ ላላ እንዴ? ይህ እኮመላነው! የበርጫ ምናምን መሸመቻ ነው እኮ?” ይላል:: አንዱ ሱፍ ይለበሰ ደግሞወገኖቸ ምን እያላችሁ ነው? ይህ እኮገንዘብነው! ባንክ አትጠቀሙም እንዴ? ብትቆጥቡ እኮ ታውቁት ነበር! ይህገንዘብነው!” ይላል:: ከሀሳቡ ይልቅ ምላሱ የሚቀድም ሌላው ደግሞኧረ ላሽ ይህ ይጠፋችኋል? ይህ እኮፍራንክነው! ቆይ ከቤተሰብ ፈልጣችሁ አታውቁም እንዴ?” ይላል:: ሌላው ባለስልጣን የሚመስል ደግሞ ቦርጩን እየገፋአይ ከእውቀት ነፃ መሆን! ይህ እኮበጀትነው! ሀገሪቱን እያንቀሳቀሰ ያለው እኮ ይህ ነው! የተለያዩ መሰረታዊ አውታሮች የሚዘረጉት እኮበበጀትነው! ” ይላል:: አንድ አባት ደግሞልጆቸ ይህ እኮመባ ወይም ምፅዋትነው! ምእመናን አስራታቸውን፣በኩራታቸውን እንዲሁም ስለታቸውን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡትመባእኮ ነው!” ይላሉ:: በዚህ መካከል ድንገት ከየት እንደመጡ ሳይታዎቅ ነጭ ፂማቸው ዠርገግ ያሉ መነኩሴ ጥሰውት ወደ መሃል ገቡ:: ሁሉም ጫጫታቸውን ጋብ አድርገው አባ ላይ አፈጠጡባቸው:: አባም በወዝ የጠገበ ቆባቸውን ዳበስ ዳበስ እያደረጉምን ሆናችኋል ልጆቸ? ይህ ሁሉ ጭቅጭቅ ምንድን ነው? ምን ተፈጠረ?” አሉና በደከመች አይናቸው ሁሉንም ቃኟቸው:: ሰዎችም በታላቅ ድምፅ መንጫጫት ጀመሩ:: አባም ጭራቸውን እያወዛወዙቆይ ቆይ ዝም በሉና እርሱ ተቀመጡ!” አሏቸውና ከፊት ለፊታቸው ድንጋይ አሸራሽተው ተቀመጡ:: ሰዎቹም ፈራ ተባ እያሉ መቀመጥ ጀመሩ:: አባምአሁን ተረጋግታችሁ አንድ ሰው ምን እንደተፈጠረ ይንገረኝአሏቸው:: ከፊት ለፊት ያለውምተሰብስበን እየሄድን እያለ ድንገት ይህን የሚያዩትን አገኘን! እረ ብር አገኘሁ ስላቸው አንዱ ጨላ ነው፣አንዱ መላ ነው፣አንዱ ገንዘብ ነው፣ አንዱ ፍራንክ ነው፣አንዱ በጀት ነው፣አንዱ መባ ነው፣ አንዱ ደምወዝ ነው ይላል! ግን እኮ አዩት አባ ብር እኮ ነው!” አለና ሁኔታውን ነገራቸው:: አባም ልብን በሚስብ ፈገግታቸው ሰዎችን ቃኝተውይህ ነው እንግዲህ “#አልተግባብቶምማለት! ልጆቸ ሁላችሁም እኮ ልክ ናችሁ! በአንድ ቋንቋ እየተናገራችሁ፥በአንድ አካባቢ እየኖራችሁ እንዴት መግባባት አቃታችሁ?” አሉና ወደ ሰዎች ተመለከቱ:: ሰዎችም ውስጥ ለውስጥ ማጉረምረም ጀመሩ:: አባም በፍቅር አይን እየተመለከቱለጆቸ ይህ ሁሉ የሆነው መሪ ስለሌላችሁ ነው:: ለዩነታችሁን አጥቦ ወደ አንድነት የሚመራችሁ መሪ! እንደ ሙሴ ለእናንተ እራሱን አሣልፎ የሚሰጥ መሪ! የሚገዛ ሳይሆን የሚመራ መሪ! እንደ መልከ ጸዴቅ እውነቱን ፈርዶ አስታርቆ የሚሸኝ መሪ! እንደ ኦዚያን በማያገባው ጥልቅ የማይል፥ እንደ ኢሳይያስ ቤቱ ሲደፈር ፈርቶ ዝም የሚል ሳይሆን ለቤቱና ለህዝቡ የሚገደው መሪ! የህዝቡን ፍላጎት እየሰማ አስሩን የሚጨብጥ ሳይሆን ህዝቡ የሚያስፈልገውን የሚሰጥ መሪ! ሐላፊነትን እንጅ ስልጣንን የማያማክል መሪ!” አሉና በረጅሙ ተነፈሱ:: ሰዎቹ ደግሞ የተመካከሩ ይመስልእኮ እኛም እርሱን እንፈልጋለን!” አሉ በአንድ ድምፅ:: አባም በተረጋጋ መንፈስ ንግግራቸውን ቀጠሉ:: “አይ እናንተ መሪ እኮ ከላይ ያለው ብቻ አይደለም::ሁሉም የመሪነት ሐላፊነት አለበት:: አገር መሪው ሀገርን፣ክልል መሪው ክልልን፣ወረዳ አስተዳዳሪው ወረዳውን፣ አባውራው ደግሞ ቤተሰቡን ግለሰብ ደግሞ ስሜቱን ሊመራ ይገባል:: አሁንም እናንተ ከሁሉም በፊት ስሜታችሁን ልትመሩ ይገባል! ስሜታችሁ እናንተን ከመራችሁ ግን የሞታችሁ ያን ዕለት ነው:: ስሜታችሁን ከልቦናችሁና ከአእምሮአችሁ ከያዛችሁ ያኔ መሪ ናችሁ መሪም ከመካከላችሁ ይዎጣል:: በሁለት አይናችሁ ክፍ ደጉን አይታችሁ በአንዱ አእምሮአችሁ ለይታችሁ መልካሙን ከመረጣችሁ፣በሁለት ጆሮአችሁ ክፍ ደጉን ሰምታችሁ በአንዱ አእምሮአችሁ ለይታችሁ መልካሙን ከወሰዳችሁ፣ ለህሌናችሁ ከተገዛችሁ ያኔ እያንዳንዳችሁ መሪ ሆናችሁ፣ ሁላችሁም ተባብታችሁ ትኖራላችሁ:: ስለዚህ ልጆቸ ያለመግባባታችሁ ምክንያት እራሳችሁን ስላልመራችሁ ነው፣ ስሜታችሁ አይምራችሁ ይልቁንም እናንተ ምሩት ያኔ አንዱ የአንዱን ሀሳብ ያዳምጣል መግባባትም ትችላላችሁ“ አሏቸውና ተሰናብተዋቸው ሄዱ:: ሰዎችም እራሳቸውን መምራት ሊጀምሩ የጠፋቸውን ልቦናቸውንና አእምሮአቸውን ፈለጋ በሃሳብ ከነፉ.................................................................................
By #melak_Teshome@KIOT


Comments