ዘወትር በልቤ

ለእናቴ
ሁሌም የማትጠፊው ዘወትር ከፊቴ
አንች ርህሩሂቷ አዛኝቷ እናቴ
ጠርቸም አልጠግብሽ ዘወትር በአንደበቴ
ስቀመጥ ስነሳ ስሄድም ስመጣ
ስቆምም ስተኛ ስበላም ስጠጣ
የአንች ትዝታ ነው ከፊቴ ሚመጣ
ዘወትር በሀሣቤ ሌላ እንዳላነሳ
ከፊቴም አጠፊ ሁሌ አንችን አረሳ
በአካል ባላገኝሽ ወደ አንች ቀርቤ
በህሌናየ አለሽ ዘወትር በልቤ
downloadd

Comments

Post a Comment