ቦታ እንቀያየር ይሆንiii??? [19/08/2010 ዓ.ም 5:27 am]
ምን እየሆንን እንደሆነ ሳስብ ግራ ይገባኛል :: ወንድ ሆኖ ተፈጥሮ ወንድ መሆን አስጠልቶት ሴት “ ለመሆን ” ይዃትናል :: ሴቷ ደግሞ ሴትነት አስጠልቷት የወንድ ልብስ በመልበስ : እንደ ወንድ በመናገር : በመራመድ : እንደ ወንድ “ አክት ” በማድረግ ወንድ ለመምሰል ትሞክራለች :: ሀገር ውስጥ ያለው ውድ ሀገሩ ኢትዮጵያ “ አስጠልታው ”: “ ወይ ኢትዮጵያ ! መቸ ይሆን የምላቀቅሽ ?” እያለ ከሀገሩ ለመውጣት ሲመኝ ያላየውን አለም ይናፍቃል :: በተቃራኒው ከሀገሩ ውጭ ያለው ውብ ሀገሩ ናፍቃው : ጋራው ሸንተረሩ፣ በጋራ መብላት መጠጣቱ፣ባህሏ፣ ቅርሷ ትዝ እያለው፣ ባርነቱ ሰልችቶት “ መቸ ወደ ሀገሬ ኢትዮጵያ በተመለስኩ ለሀገሬ አፈር ባበቃኝ !” ይላል :: በቅድስት እምነት ኦርቶዶክስ ውስጥ ያለው በእምነት በምግባር መቆየት “ ሰልችቶት ” ወደ መናፍቃን አዳራሽ ይጎርፋል :: እኩሉ ደግሞ አእምሮውን ሽጦ የሚኖርበት እምነት _ ቅብ ስጋዊ ሕይወት ሰልችቶት ወደ ቅድስት እምነት ይመጣል :: በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ ያለው ደግሞ በዝማሬ፣ በፀሎት የኖረው መዝሙር “ ሰልችቶት ” ዘፈን ዘፈን እያለ ወደ አለም ይወጣል :: በዘፈንና በዳንኪራ የቆየው ጫጫታውና ሙዚቃው ሰልችቶት መዝሙርና ፀሎት ናፍቆት፣የተመስጦ ሕይወት መኖር ተመኝቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጣል :: ሰባኪው የተቀበለውን መክሊት ረስቶ ዘረኝነት አስክሮት፣ ፖለቲካው አስጥምሞት መክሊቱን ይቀብራል :: ፖለቲከኛው ደግሞ ክርክሩ፣ ንዝንዙ፣ አድርባይነቱ ሰልችቶት ሁሉንም ጠጥሎ ወደ...