Posts

“ደስ ሲል!”

ፊቱ ቅጭም ብሎ አንገቱን ደፍቶ በቀስታ ከአዳራሹ ወጣ :: የለመደው አዳራሽ ስለሆነ ብቻ እግሩን እያነሳ እይጥለዋል እንጅ ወዴት እንደሚሄድ እንዴት እንደሚራመድ አያውቀውም :: ዳዊት ከአዳራሹ ከወጣ በኋላ ዘወር ሲል አይኑን ከባነሩ ጋር አፈጠጠና “ ኦርቶዶድሳዊ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አስተምሮዋን እንጠንቅቅ፣ ድርሻችንን እንወቅ ” የሚለውን አነበበና ፍርጥም አለ :: ዳዊት ከቤተ ክርስቲያን መልስ ቁርሱን ከበላ በኋላ ማህበረ ቅዱሳን ኮምቦልቻ ወረዳ ማዕከል ያዘጋጀውን 5 ኛውን ልዩ አውደሪ ለማየት ትኬቱን ቆርጦ ሲገባ ባነሩን እንዴት እንዳላስተዋለው ገረመው :: “ መልዕክቱኮ ከባነሩ አለ ” አለ ለራሱ :: ትንሽ እንደተጓዘ ከፅዱ ስር ቁጭ አለ :: ድንገት ጓደኛው መለሰ ከፊቱ ቆሞ “ ዳዊት ምን ሆነሃል ? ፈዘ ሃ ል እኮ !” አለው :: ዳዊትም “ አውደሪው እንዴት ነበር ?” አለው ለስለስ ባለ ድምፅ :: መለሰም “ ደስ ይላል ! አንተ ! አቅራቢዎችን አየሃቸው ? አቤት ብቃት ! አለባብሳቸው ሲያምር አንተ ! ደግሞ እኮ አይሳሳቱም ! ኧረ በስመ አብ ! ደስ ይላል !” አለው :: ዳዊትም በመገረምና በመናደድ ስሜት ትኩር ብሎ ይመለከተው ነበር :: ዳዊትም ከፊቱ የቆመውን መለሰን ከቁብ ሳይቆጥር በሀሳብ ደመና ተጭኖ መብረር ጀመረ :: “ ለካስ እስከ ዛሬ ስህተት ነበርኩ ! ለምን ፓትሪያሪኩ ይህን አያደርጉም ? ጳጳሱ የት ሄ ደው ነው ? መምህሩስ ? ሰበካ ጉባኤው ምን እየሰራ ነው ? የግቢ ጉባኤ ስራ አስፈፃሚዎች ምን ሆኑ ? ወዘተ ........ ያልሁት ለካስ ...